የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በባህር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል (13-04B) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የውሃ ስርገት ጥገና (Membrane type Water Proofing Maintenance Work) ሥራ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በባህር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል (13-04B) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የውሃ ስርገት ጥገና (Membrane type Water Proofing Maintenance Work) ሥራ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የዕቃው (ሥራው) አይነት
|
የፕሮጀክቱ ስም
|
የጨረታ ቁጥር
|
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት
|
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
1
|
የውሃ ስርገት ጥገና (Membrane type Water Proofing Maintenance Work)
|
ሪፈራል ሆስፒታል (13-04B) ፕሮጀክት |
DCE/13-4B/001/2025
|
ህዳር 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል |
ህዳር 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ይታሸጋል |
50,000.00
|
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሠማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሠ የንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ፣ የምስከር ወረቀትና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታክስ የምስክር ወረቀት (ታክስ ከሊራንስ) እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ60 (ስልሳ) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ወራሚት ቀበሌ በሚገኘው ሪፈራል ሆስፒታል አቅና ግዥ ቡድን ቢሮ መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት እንዲሁም በሳይት ምልከታ ወቅት ግንዛቤ ውስጥ ያስገቡትን የጥገና ሥራ መሠረት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሳይት ምልከታ በማድረግ ጥገናውን የሚያከናውኑበትን የአሠራር መንገድ (Detail Work Methodology) በዝርዝር ማዘጋጀት አለባቸው።
- ጨረታው በሰንጠረዥ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ አቅ/ እና ግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
አድራሻ፡- |
ባህር ዳር ሪፈራል ሆስፒታል ፕሮጀክት ወራሚት ቀበሌ ወደ መኮድ ም/ዕዝ መታጠፊያ መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር 09 86 89 46 35 / 09 18 08 87 59
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
