በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ 5ኛ ደረጃ ዕጣን ምርት 180ኩ/ል እና በቻግኒ ቅርንጫፍ 5ኛ ደረጃ ዕጣን ምርት 125ኩ/ል በድምሩ 305ኩ/ል የዕጣን ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ የዕጣን ምርቶች ሽያጭ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - የግ/ው/ሽ/ሜ/አ/ዘ/ግጨ ሸ01/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ በአዳማ ቅርንጫፍ 5ኛ ደረጃ ዕጣን ምርት 180ኩ/ል እና በቻግኒ ቅርንጫፍ 5ኛ ደረጃ ዕጣን ምርት 125ኩ/ል በድምሩ 305ኩ/ል የዕጣን ምርቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል እና በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት በመንግስት ግዥ አቅርቦት የተመዘገበ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽ የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። የዕጣን ምርቶች ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል።
- ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት በኢግሥኮ-የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ህዳር 11/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው ዝርዝር ምርቶች ውስጥ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይቻላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ 011 666 2390
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ
