Tender Detail

Tender Details


አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የቢሮ ማሽኖች እና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር/003/2018

                             ግልጽ ጨረታ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ከዚህ በፊት ይጠቀምባቸው የነበሩ ያገለገሉ ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ የቢሮ ማሽኖች እና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ-ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 – 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 230.00 (ሁለት መቶ ሰላሳ ብር) ከባንኩ ዋና መ/ቤት ስር በሚገኘው የካ ቅርንጫፍ በመክፈል ከሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት በሰንጠረዡ በተጠቀሰው መሰረት ይሆናል፡፡
ተ.ቁ የእቃው አይነት የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት
1 ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች  

ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

ከቀኑ 8፡00

 

ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15

2 የቢሮ ማሽኖች
3 የቢሮ ፈርኒቸሮች
4 ሌሎች

 

  1. ከጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ በክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ስም አሰርተው በታሸገ ኢንቬሎፕ ከነሙሉ አድራሻው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

 

  1. ማንኛውንም ተጫራች የሚገዛውን የንብረት አይነት በመጥቀስ በባንኩ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ሞልቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  2. የጨረታው መወዳደሪያ ሰነድ ግልፅ እና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ የተደረገበት ዋጋ ከሆነ በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ፈራሚ አካል ፓራፍ/ኢንሺያል ፊርማ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል እንዲሁም ከቫት በፊት እና በኃላ መሆኑ መግለፅ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ንብረቶቹን ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 – 10፡00 እና ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30- 5፡30 ቀደም ብሎ ቀጠሮ በማስያዝ ቃሊቲ በሚገኘው የአንበሳ ኢንሹራንስ ሪከቨሪ ጊቢ ውስጥ፣ ከደራርቱ አደባባይ ወደ አያት ጣፎ በሚወስደው መንገድ ከለሚ ኩራ ፖሊስ ጣቢያ ከፍ ብሎ እና ቦሌ መድኃኒዓለም ማፊ ሞል አጠገብ በሚገኘው የባንካችን ህንፃ ቤዝመንት ወለል ማየት ይቻላል፡፡
  5. ጨረታው 22 አካባቢ የቀድሞ ዘሪሁን ህንፃ ፊት ለፊት ሌክስ ፕላዛ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በአንበሳ ባንክ ዋና መ/ቤት 4ኛ ወለል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ በመፈፀም ያስያዙትን ሲፒኦ (CPO) መውሰድ የሚችል ሲሆን ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 3 (ሶስት) የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ለባንኩ ከፍለው ንብረቱን በ3 ቀናት ውስጥ መረከብና ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. በተባለው ጊዜ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉም ሆነ ገቢ አድርገው ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ /ሲፒ.ኦ/ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንደ አስፈላጊነቱ ለሁለተኛ አሸናፊ ወይም በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ለተጫረቱበት ንብረት ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላሉ፡፡
  10. ስለእያንዳንዱ ንብረት ዝርዝር እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዋናው መ/ቤት ግዥ እና ፋሲሊቲስ ማኔጅመንት መምሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0116-36-20-64/ 0919768134/ 0913581240/ 0923789251 ማግኘት ይቻላል፡፡
  11. ባንኩ ስለንብረቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሽያጩን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                   አንበሳ ባንክ አ.ማ

                      ዋና መ/ቤት

Save Tender