በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በእያንዳንዱ የጣውላ ዓይነት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጣውላ ምርት ግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር OFWE/XA04 /2018
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት በእያንዳንዱ የጣውላ ዓይነት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
- በአርሲ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፣
- በጅማ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፣
- በባሌ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፣
- በቦረና ጉጂ ቅጽ ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያዎች ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፣
- በፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ጣውላ፣
- በሐረርጌ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ጣውላ፣
- በኢሉአባቦራ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፣
- በወለጋ ቅ/ጽ/ቤት የእንጨት በተለያዩ የእንጨት መሰንጠቂያ ላይ የተዘጋጀ ጣውላ፣
በመሆኑም
- የጣውላ የቤትና የቢሮ እቃዎችና ተዛማጅ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም Tin number ያላቸውና እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል አይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 እና ጨረታው በሚወጣበት በጂማ ቅ/ጽ/ቤት (ዲማ) በኢሉአባቦራ ቅ/ጽ/ቤት (መቱ) በአርሲ ቅ/ጽ/ቤት (አርሲ ነጌለ) ፊንፊኔ ቅ/ጽ/ቤት (ፊንፊኔ) በሐረርጌ ቅ/ጽ/ቤት (ጭሮ) በቦረና ጉጂ ቅ/ጽ/ቤት (አዶላ) በባሌ ቅ/ጽ/ቤት (ጎሳ) በወለጋ ቅ/ጽ/ቤት (ግምቢ) በመግዛት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bld bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የምትጫረቱ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በቅ/ጽ/ቤት የምትጫረቱ መ/ቤቱ ከሚገኝበት ከተማ በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (cpo) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111240249 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
