በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብረካ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል መጠኑ 82,000 (ሰማንያ ሁለት ሺህ) ቶን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሀገር ውስጥ ጨረታ ቁጥር
ሙሲፋ/03/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብረካ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል መጠኑ 82,000 (ሰማንያ ሁለት ሺህ) ቶን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ወይም አቅራቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸው አምራች ከሆናችሁ ከክልል መንግስታት የተሰጠ የማዕድን ማምረት ስራ ፍቃድ ሰርተፊኬት አቅራቢ ከሆኑ የአቅራቢነት ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ የድንጋይ ከሰል ምርመራ ውጤት እና ይዞታ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ (አስገዳጅ መስፈርት ሲሆኑ አሟልቶ ያላቀረበ ከጨረታው ይሰረዛል) ስለዚህ የተመቀሱትን ማስረጃዎች፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስና የታክስ ከፋይ ምዝገባ ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመልስ ብር 575.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊየን ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብረካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም ባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
ስልክ 0114420216
ፋክስ 0114420688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
