የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የጨረታ ሎቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት
ሎት 2 የዲኮር ግብዓቶች እና ሌሎች አገልግሎቶች በኪራይ
ሎት 3 የህትመት ስራዎች
ሎት 4. የፕሮቶኮል ልብስ
ሎት 5. የሃገር ባህል ልብስ
ሎት 6. የተፈጥሮ ውሃ
ሎት 7. የተለያዩ የመኪና ጎማና ዲኮር ዓይነቶች
ሀ/ የተለያዩ የመኪና ዲኮር ዓይነቶች
ለ/ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች
ሎት 8 ICT እቃዎች
ሎት 9 የፕሪንቴር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች
ሎት 10 የፅሕፈት መሣሪያ
ሎት 11. የደንብ ልብስ
ሎት 12. የፅዳት እቃዎች
በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 በመክፈል ሰነዱን ከግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 105 1ኛ ፎቅ መግዛት ይቻላል።
1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቼክ ወይንም በባንክ CPO 2% ከአጠቃላይ ዋጋ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% (አሥር በመቶ) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነድ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻው በየገፁ ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት፤ ይህ ሳይሆን ሲቀር መ/ቤቱ ቫት እንደተካተተ አድርጎ ይወስዳል።
6. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
7. በሎት 4፣ በሎት 7፣ ሎት፣ ሎት 9፣ ሎት 10፣ ሎት 11 እና ሎት 12 የምትወዳደሩባቸውን ናሙና መቅረብ አለበት።
8. ተወዳዳሪዎች ለተመሳሳይ አገልግሎት ተመሳሳይ ዋጋ ካቀረቡ በዕጣ የሚለይ ይሆናል።
ለሎት 3 የህትመት ዓይነቶች ለምትሳተፉት
* ጥራታቸውና የቴክኖሎጂ ደረጃቸውን የጠበቁ በአጭር ሰዓት ውስጥ መድረስ የሚችል የህትመትና የማስታወቂያ ስራዎች ለመስራታቸው ማረጋገጫ የሚያቀርብ
* የሚያቀርቧቸውን የህትመትና ማስታወቂያ ስራዎች በ/ጽ/ቤቱ የቴክኒክ ኮሚቴ ጥራታቸውና ዘመናዊነታቸውን ለማረጋገጥ ማሳየት የሚችሉ።
* ወቅቱን የሚመጥኑ ዘመናዊ ማሽኖች ያሏቸውና ለትልልቅ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ሁኔቶች ልዩ ልዩ የህትመትና የፕሮዳክሽን ስራዎችን የሰሩ ስለመሆናቸው መረጃ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
9. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. አሸናፊ ድርጅት ውል ከተዋዋለ በኋላ ዋጋ መጨመርና መቀነስ የማይቻል መሆኑ፤
13. መ/ቤቱ ከተገኘው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% የእቃውን ወይም አገልግሎቱን መቀነስ ወይም መጨመር የሚችል መሆኑን።
14. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ
አድራሻ፡- ካሳንቺስ ልማት ባንክ ጀርባ
የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች፡-
1. የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የምሥክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. በሎት 1 የሚወዳደሩ በሥራ ዘርፉ ለመሰማራታቸው የብቃት መረጋገጫ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት
