የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የኤርሳይድ የመሬት አቀማመጥ የውሃ ምንጭ እና ልማት ሥራዎች ዲዛይን ግምገማ፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት የሚሰጡ የሀገር ውስጥ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሀገር እና የሀገር ውስጥ ደረጃ, የውሃ ሀብት ምህንድስና አማካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ SSNT – T584
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የኤርሳይድ የመሬት አቀማመጥ የውሃ ምንጭ እና ልማት ሥራዎች ዲዛይን ግምገማ፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት የሚሰጡ የሀገር ውስጥ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሀገር እና የሀገር ውስጥ ደረጃ, የውሃ ሀብት ምህንድስና አማካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ አማካሪዎችን ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ ለዲዛይን ሥራ 90 ቀናትን ጨምሮ በ420 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይሆናል።
ከላይ ለተገለጸው ፕሮጀከቶች ከዲዛይን ግንባታ ተቋራጭ ጋር የመግባቢያ ስምምነት (Mou) ያላቸው ተጫራቾች በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም።
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብርእዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 1 2018 ባሎት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E99) ለኢትዮጵያ እየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T584 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላከ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት መቶ ሺህ ብር (200,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ታኅሣሥ 1 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ እየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡ 30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር Tel: +251 115 17 4028/8025 / ኢ-ሜይል፡AynalemAy@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበ ነው።
