በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ቧንቧና መገጣጠሚያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ቧንቧና መገጣጠሚያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ያለው /ያላት/
2. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፊቃድ የሚያቀርብ
3. ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን እየተወጡ ያሉና በጨረታው ተካፋይ መሆን እንደሚችሉ የሚገልፅ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርብ።
4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን
5. የድርጅቱ ማሕተም በፖስታው ላይ እና በጨረታ ሰነዱ ላይ እንዲያርፍበት ይገደዳል።
6. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራቾች ሙሉ ስም እስከ ፊርማ መኖር አለበት።
7. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ መስከበሪያ የሚሆን 2% በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያዉ ከቀረበዉ ዝርዝር ድምር በታች ከሆነ ከጨረታዉ ዉጪ እንደሚሆኑ እንገልጻለን።
8. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፈው ድርጅት የውል ጠቅላላ ዋጋ 10% ለሥራ አፈጻፀም ዋስትና በቅዲሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታዉን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታዉ ውጪ እንደሚሆኑና ለጨረታ ማስከበሪያ ያያዙትን ገንዘብ የማይመለስ መሆኑን እንገልጻለን።
10. ተጫራቾች ቧንቧና መገጣጠሚያዎችን የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሠነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በግልጽ በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒውን በስም በታሽገ ኤንቨሎፒ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ቴፒ ከተማ ዉሃ አገልግሎ ኢንተርፕራይዝ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቴፒ ከተማ ዉሃ አገልግሎት ጽ /ቤት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። በዕለቱ በዓል (ዝግ) ከሆነ በቀጣዩ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
11. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከቴፒ ከተማ ዉሃ አገልግሎት ጽ/ቤት በመቅረብ ለእያንዳንዱ ግዥ የማይመለስ ብር 500 /ብር አምስት መቶ/ በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለ።
12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን የቧንቧና፤ መገጣጠሚያ እስከ ቴፒ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገት ድርጅት በራሱ ትራንስፖርትና ወጪ ይዞ በማምጣት ማስረከብ አለበት። ቧንቧ እና መገጣጠሚያ ተጫርቶ ያሸነፈው ድርጅት የዕቃዉ ናሙና ማቅረብና በናሙናዉ የጥራት ደረጃ መሠረት ማቅረብ ይኖርበታል ። ካቀረበዉ ናሙና ዉጪ ያቀረበ አሸናፊ ድርጅቱ ዕቃዉን የማይቀበል ይሆናል።
13. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 23 43 04 11 / 09 17 12 67 20 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
