Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
  • Address ሀዋሳ ከተማ አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-212-13-34
  • Website
  • Deadline07 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 500 (አምስት መቶ ብር)
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Categories Building Materials , Traffic Signs and traffic light , Road Stud , different Safety tools and Safety roller

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይናንስ መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድውን ደረጃ የሚመጥነውንሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል አጫርቶ ማሰራትን ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይናንስ መምሪያ በሀዋሳ ከተማ አስ/ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በከተማ ውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር የሚተከል ምልክትና ማመላከቻ ሳህንና የሚቆመውን ብረት የከተማውን ደረጃ የሚመጥነውን ለማሰራት ስለተፈለገ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ ለማሰራት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል አጫርቶ ማሰራትን ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት:-

  1. በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች -
  2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው በጨረታው እንዲሳተፉ የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
  5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ / የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ(CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
  7. በቂ መረጃ ከሰነዱ ማግኘት እንደምትችሉ እናረጋግጣለን፣
  8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋይ ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር - 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
  10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Open tender for manufacturing and supplying road signs, signposts, and related safety materials for Hawassa City's internal roads. Eligible bidders must hold a valid trade license, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
Save Tender