በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ወለጋ ዞን በጎቡ ሰዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም ለተለያዩ ሴክተሮች የሚውሉ የቢሮ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ወለጋ ዞን በጎቡ ሰዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም ለተለያዩ ሴክተሮች የሚውሉ የቢሮ ዕቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት የጽሕፈት መሣሪያ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ የግንባታ ዕቃዎች የደምብ ልብስ የመኪና ጎማ እና ፈርኒቸሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-
1. ተወዳዳሪው በዘርፉ ፍቃድ ያለውና የ2019 ግብር የከፈለና ንግድ ፍቃዱ የታደሰ መሆን አለበት ።
2. ተወዳዳሪው ንግድ ፍቃዱን ኦርጅናልና ኮፒውን እንዲሁም ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለበት።
3. ተወዳዳሪው የጨረታው ሰነድ ከ21/12/2018 ዓ.ም እስከ 4/01/2019 ዓ/ም ሁልጊዜ በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 11፡30 ቤጎቡ ሰዮ ወረዳ ገቢዎች ቢሮ የቢሮ ቁጥር - በሆነ ሰነዱን በማይመለስ 300 ብር ከፍሎ መግዛት ይችላሉ።
4. ተወዳዳሪዎች በሚፈለገው ዝርዝርና ጥራቱን ጠብቆ ማቅረብ ግድ ነው።
5. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 በቼክ በተረጋገጠ CPO ባንክ ማስያዝ አለበት። ይህን የጨረታ ማስከበሪያ ለተሸናፊው ነጋዴ ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን ለአሸነፈው ነጋዴ ደግሞ ውል ተፈርሞ ዕቃ እስከሚቀርብ ድረስ ይቆያል።
6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን 4/1/2019 ዓ.ም ሆኖ በዚሁ ቀን 3:30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
7. ጨረታውን ያሸንፈ ተወዳዳሪ ወይም ነጋዴ በራሱ ትራንስፖርት ማውረጃና መጫኛ ችሎ እስከ ጎቡ ሰዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ማቅረብ አለበት፡፡
8. ማንኛውም ተወዳዳሪ አንዱ ባስገባው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማስገባት አይችልም።
9. ጨረታውን የተሻለ ዋጋ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል።
ማሳሰቢያ፡- ተወዳዳሪዎች ሕጋዊ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 20 42 13 65/ 09 23 91 46 37 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በምሥራቅ ወለጋ ዞን የጎቡ ሰዮ ወረዳ ገንዘብ
ጽ/ቤት
