Tender Detail

Tender Details

  • Company በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ጤና ጣቢያ
  • Address መካኒሳ አቦ መዞሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ /ፒስ ህንጻ/ ወደ ውስጥ 400 ሜትር ገባ ብሎ 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 403 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113692872
  • Website
  • Deadline10 Sep 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 120/አንድ መቶ ሃያ ብር/
  • opening dateበቀጣዩ ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning & Janitorial , Health Care, Medical Industry

በልደታ ከፍለ ከተማ ስር የሚገኘው ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ 1ኛ

በልደታ ከፍለ ከተማ ስር የሚገኘው ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል የፈርኒቸር ዕቃዎች፤ የህከምና ዕቃዎችና ሪኤጀንቶች፤ የፅዳት ዕቃዎች፤ የኤሌከትሮኒከስ ዕቃዎች ፤ጥገና፣ የፅህፈት ዕቃዎች፣ ደንበ ልብስ፣ የህትመት ስራዎች ስለሆነም ተጫራቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

1.     ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር /Suppliers list መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ከመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የምስከር ወረቀት እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 120/አንድ መቶ ሃያ ብር/በመከፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ግዢ ከፍል በአካል ቀርቦ መግዛት ይቻላል፡፡

3.    የጨረታ ማስከበሪያ ለህከምና ዕቃ ብር 20,000/ሀያ ሺህ ብር/ እና ሪኤጀንት ብር 20,000/ሀያ ሺህ ብር/ ፈርኒቸር ዕቃ 20,000 /ሀያ ሺህ ብር ለጥገና 20,000(ሀያ ሺህ ብር ) ለኤሌከትሮኒከስ 20,000(ሀያ ሺህ ብር ) እና ለሌሎች ለያንዳንዳቸው ሎት 5000 ብር /አምስት ሺህ ብር/ በባንክየተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4.    ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ዝርዝር ዋጋና መለያ ቁጥር በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማህተም ና ፊርማ በማኖር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ(የተሞላ ሙሉ ሰነድ)4ኛ ፎቅ ግ/ን/አስ/ደጋፍ የስራ ሂደት ባለው በታሸገ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5.    የመወዳደሪያ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ለዋጋ መስጫ በተዘጋጀው ቦታ ያለ ቫትና ከቫት ተለይተው መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡

6.    ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ሁለት ቀናት በፊት ኦርጅናል እና ደረጃቸውን የጠበቁ ናሙና በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ሜዲካል ዳይሬክተር ቢሮ አጠገብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

7.    የጨረታው ሳጥን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበትን 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአሥረኛው ቀን በ11፡ዐዐ ሰዓት ታሽጎ በቀጣዩ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሳጥን መከፈቻ ሥነ-ስርዓትን አያጓትትም፡፡

8.    መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ ግዥ/ን/ጠ/አገ/የስራ ሂደት፡፡ 4ኛ ፎቅ ሳይ ቢሮ ቁ403

አድራሻ ፡- 0113692872 መካኒሳ አቦ መዞሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ /ፒስ ህንጻ / ወደ ውስጥ 400 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 04

 

በልደታ ክፍስ ከተማ ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ ጤና ጣቢያ

 

✨ messages.ai_summary
Procurement of furniture, medical supplies and reagents, cleaning items, electronics, maintenance, office supplies, uniforms, and printing services for District 04 Health Station. Bidders must hold a renewed trade license, be registered on the government suppliers list, and provide VAT registration proof.
Save Tender