የሚ/አ/ ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ግብርና ጽ/ቤት አገ/ት የሚውል የእንስሳት መድኃኒት በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚ/አ/ ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ግብርና ጽ/ቤት አገ/ት የሚውል የእንስሳት መድኃኒት በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከሚመለከተው አካል በዘርፉ የተሰጠ የታደሰ የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ ከግዥ ክፍ/ንብ/አስ/ር ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን /በነጻ/ በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ ሞልተው ሲመልሱ ህጋዊነት ሰነድ እና ፋይናንሻል የተሞላበትን ሰነድ 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 /አምስት ሺህ/ ብር ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ቼክ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ለሚ/አ/ከ/አስ/ር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በማለት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ3፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው
- በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የቃላት ወይም የትርጉም ስህተት ቢኖር በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው የበለጠ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ /ኢ/ል/ ጽ/ቤት
