Tender Detail

Tender Details

  • Company የበቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር
  • Address በጅማ መንገድ ከአዲስ አበባ 80ኪ.ሜ ቱሉ ቦሎ ከተማ ፡ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113420140
  • Website
  • Deadline28 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-11-28 00:00:00
  • Categories Machinery , Office Machines And Computers

በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ እና አዲስ የፋብሪካ ማሽኖች እና የተለያዩ አይነት ያገለገሉ ኮምፒውተሮች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::


ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን የተለያየ ዓይነት ያገለገሉ እና አዲስ የፋብሪካ ማሽኖች እና የተለያዩ አይነት ያገለገሉ ኮምፒውተሮች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም መግዛት የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች በማሟላት ተወዳድሮ መግዛት ይችላል::

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የአመቱን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል::

2. ለጨረታ ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት) በዩኒየኑ የባንክ ሂሳብ ቁጥር

1000087184327 ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንከ ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ

1000036818348 በመከፈል ሰነዱን ከዩኒየን መውሰድ አለባቸው::

3. ለጨረታ ማስረከቢያ ቢድ ቦንድ ማስያዣ ያቀረቡትን ዋጋ 5% በሲፒኦ ወይም በባንክዋስትና ሰነድ ማስያዝ አለባቸው::

4. ተጫራች የጨረታ ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 19/03/2018ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዩኒየኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ::

5. የጨረታ መክፈቻ ቀን 19/03/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::

6. ተጫራቾች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው::

7. ዩኒየኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን ንብረት ሙሉ በሙሉ እስከ 10 ቀን ጊዜ ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል::

አድራሻ፡- በጅማ መንገድ ከአዲስ አበባ 80ኪ.ሜ ቱሉ ቦሎ ከተማ ላይ እንገኛለን::

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልከ ቁጥር 0911080003/0912122971 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::

የበቾ ወሊሶ የገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒየን

Save Tender