ድርጅታችን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ የሳኩራይ ባለ 4 ዩኒት ማሽን የጥገና የአገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው በዘርፉ የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሽኑን ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
የሳኩራይ ባለ 4 ዩኒት ማሽን የጥገና አገልግሎት
ግዥ ግልጽ ጨረታ ቁጥር EMPDE/NCB/10/2018
ድርጅታችን የሳኩራይ ባለ 4 ዩኒት ማሽን የጥገና የአገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ብቃት ያላቸው በዘርፉ የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሽኑን ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
1. በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፍኬት መሆኑን።
2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10:30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
5. ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የድርጅቱ አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ታጥፎ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር /0116 -46-34 81 መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት
