Tender Detail

Tender Details

  • Company Geda Transport and Logistics S.C. (ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ አ.ማ)
  • Address ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮልጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 558 25 19
  • Websitehttps://www.gedatransport.com/#
  • Deadline08 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-08 00:00:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products , Materials

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጭነት ማሰሪያ ካቦ እና ገመድ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/07/2018

 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲ አ. የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጭነት ማሰሪያ ካቦ እና ገመድ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘርፉ የተሰማሩ ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስ እና ሌሎች አስፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን የር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12 ፎቅ ከጠዋቱ 230 እስከ 1100 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ማህተም በማድረግ እና በመፈረም በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያዬ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም፡፡
  7. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
  8. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ 16ኛው ቀን 800 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 830 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. የጨረታ ፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

አድራሻ፡- ሰንጋ ተራ ንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 2 ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-558-25-19

 

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ .

 

Save Tender