Tender Detail

Tender Details

  • Company SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5 51 91 00
  • Websitehttps://www.filwuha.gov.et/
  • Deadline16 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-16 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Maintenance And Repair

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ እቃ ግዥ /አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ እቃ ግዥ /አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በዚህም፦

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ/ የአገልግሎት ግዥ

ሎት 1 የሙቅ ውሃ ጉድጓዶች የጥገና ሥራ አገልግሎት ግዥ

ሎት 2 ዛላ በርበሬ ግዥ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ 2017/2018 . ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00/ሃምሣ ሺህ ብር/እና ለሎት 2 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

4 ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመከፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት፡፡

7. ጨረታ በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚስረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይስረዛል፡፡

8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡

9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በስም በታሸገ ኤንቨሎኘ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡

10.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታው ቴክኒካል ኘሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

11.የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምገማ ለሎት 1 ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት እስፔስፊኬሽን /Specification/ ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) እና ለሎት 2 ቴክኒካል ናሙና ግምገማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምግማ ውጤት (60%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን እስፔስፊኬሽን /Specification/ ግምገማ ወይም የናሙና ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሰነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር 0115 53 07 67/0115 15 73 37

ፍልውሃ አገልገሎት ድርጅት

Save Tender