Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa Traffic Management Authority (AATMA) (የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን)
  • Address ሃያ ሁለት መክሊት ሕንፃ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-01 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251116672279
  • Websitehttps://aatma.gov.et/
  • Deadline09 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-12-09 00:00:00
  • Categories Office Equipment

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የንብረት መደርደሪያ የብረት ሼልፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አአትማባ /ብግጨ/ ግዳ/ ዕቃ/06/2018

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የንብረት መደርደሪያ የብረት ሼልፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

በመሆኑም ፦ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ፦

1. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) የማይመለስ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በባለስልጣኑ ግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎትዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10-01 መውሰድ ይችላሉ::

2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለሚያቀርቡት አገልግሎት ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች በአቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼከ (ሲፒኦ) ተመላሽ የሚሆን 100,000.00 (መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡

5. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡት ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በባለስልጣኑ ግዥ ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዋና ከፍል በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም በማስያዝ እና ውል መፈረም አለባቸው፡፡

6. የጨረታው አሸናፊ ላልሆኑ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡

7. ጨረታው ህዳር 30/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡

8. ጨረታው ህዳር 30/2018 ዓ/ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ታጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

9. ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

10. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በተመለከተ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ስድራሻ፡- ሃያ ሁስት መከሲት ህንፃ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-01 ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልገዎ በስልክ ቁጥር

0116-672-342 ማነጋገር ይችላሉ::

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

Save Tender