Tender Detail

Tender Details


የቡዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቦቹ ፋውንዴሽን (BTFF) በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግብዓቶችና የተለያዩ ሥራዎችን በግልጽ ጫራታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡


የቡዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቦቹ ፋውንዴሽን (BTFF) በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን ፈቃድ ቁጥር 4381 ተመዝግቦ የተቋቋመ ከፖለቲካ እና ከሃይማኖት ነፃ የሆነ  ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው። በኢስት አፍሪካ ሆልዲንግስ አክሲዮን ማህበር (EAHSC) የተመሰረተው ይህ ፋውንዴሽን በድህነት ቅነሳ፣ በትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በጤና አጠባበቅ እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊ ፈተናዎችን ለመቀነስ አልሞ ይሠራል::

በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግብዓቶችና የተለያዩ ሥራዎችን በግልጽ ጫራታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡

  • የ2019 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
  • የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
  • የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
የምድብ ምድብ (Lot Category) ከእርስዎ የግዢ ዝርዝር የተካተቱ ዕቃዎች
ምድብ 1: የሲቪል ግንባታ ሥራዎች •  የመጸዳጃ ቤት እና የሻወር ግንባታ (ለሚ – እንሳሮ ወረዳ)

•  የሥልጠና ማዕከል ግንባታ (ድሬዳዋ)

•  የሆስፒታል አጥር ግንባታ (ለሚ – እንሳሮ ወረዳ)

•  የመኪና ማቆሚያ ግንባታ (ለሚ – እንሳሮ ወረዳ)

ምድብ 2: ለምገባ ፕሮጀክት የሚሆኑ የምግብ ግብዓቶች •  የበዓል አቅርቦቶች (ዶሮዎች እና የምግብ ዘይት ባለ 5 ሊትር)

•  የአጃ ቂንጬ

•  የበቆሎ ቂንጬ

•  ቦሎቄ

•  ጨው

•  የምግብ ዘይት ባለ 20 ሊትር

•  ሩዝ እና የስንዴ ዱቄት

ምድብ 3: ኤሌክትሮኒክስና መሸኖች •  ፍሪጅ

•  የሣር ማጨጃ ማሽን

ምድብ 3: የጽዳት እና ሳኒተሪ አገልግሎት ግብዓቶች •  የጽዳት መሣሪያዎች (መጥረጊያዎች፣ የሽንት ቤት/የወለል መወልወያዎች፣ ቫክዩም ክሊነሮች፣ ፍሊት/ብሎወሮች፣ ባልዲዎች፣ ማጠቢያዎች)

•  የጽዳት ኬሚካሎች (ዴቶል፣ በሊች/በረኪና፣ ሳሙናዎች፣ ማጽጃዎች፣ አልኮል)

•   የግል ደህንነት መጠበቂያዎች (PPE) እና የቆሻሻ ማስወገጃ ቁሳቁሶች

ምድብ 4: የአረንጓዴ ልማት ·   የዛፍ ችግኞች፣ አበቦች እና ኮምፖስት (ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ)
ምድብ 5: የሥራ ልብሶች እና የደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶች (PPE) •  የሥራ ቱታ

·   የደህንነት ጫማዎች እና የእጅ ጓንቶች

ምድብ 6: የቢሮ እቃዎች፣ ስቴሽነሪዎች እና ፈርኒቸር •   ላፕቶፖች

•   ፕሪንተር እና ተዛማጅ ግብዓቶች

·   የሕትመት ወረቀት እና ሌሎች ተዛማጅ ግብዓቶች

·   ኪችን ካቢኔት

  1. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ዘወተር በሥራ ሰዓት በቢሯችን ተገኝተው የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት (ከቀኑ 8:00) ይዘጋል።
  4. ጨረታው መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋውንዴሽኑ ቢሮ ይከፈታል።
  5. ፋውንዴሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዶ/ር ኪሩቤል ግርማይ/ማህሌት በሱዬ

ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ካምፖኒ ዋና መስሪያ ቤት

ጦር ኃይሎች አዋሽ ወይን ፋብሪክ በስተጀርባ፣ የኢስት አፍሪካ ልዲንግ ሕንጻ ስባተኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 0912118437/0940110868

Save Tender