ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፀውን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፀውን እቃ/አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
በድጋሚ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ የአገልግሎት ግዥ
ሎት 1 የታረደ የሐበሻ ዶሮ አቅርቦት ግዥ
ሎት 2 የእሳት አደጋ መከላከያና ማጥፊያ ስሊንደሮች ሙሌት ግዥ
ሎት 3 የአጥንት መቁረጫ /Bon Cutter/
ሎት 4 የድንች መጥበሻ ማሽን /Deep Fryer/
ሎት 5 ቨርቲካል ፓምፕ Nertical Pump/
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች በማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው
1. ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017/2018 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው የገቢዎች ከሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገርውስጥ ገቢ የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርበአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገበና የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 እና 2 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) እና ለሎት 3፣ 4 እና 5 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው::
4. ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የሚስጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው::
6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ሰለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መግለጽ አለበት፡፡
7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሣስ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴከኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid document/ መስረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋላ፡፡ የጨረታው ቴከኒካል ኘሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ማስገባ አለባቸው፡፡
11.የጨረታ ሂደቱ የቴከኒክ ግምገማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ለሎት 1 እና 2 ቴከኒካል ሠነድ ግምገማ ናሙና ወይም ድርጅታዊ ብቃት ግምገማ ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (40%) እና ለሎት 3 ፣ 4 እና 5 የቴከኒክ ግምዢማ ወይም እስፔስፊኬሽን /Specification/ ግምገማ ውጤት (55%) እና የፋይናንሺያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (45%) ሲሆን ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ግምገማ እና እስፔስፊኬሽን/Specification/ግምገማ ሰነድ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ፤ ናሙናውን ወይም ድርጅታዊ ብቃት እና ቴክኒካል ግምገማ ሠነድ ወይም የግምገማ ብቃት ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሠነድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፦ ስልከ ቁጥር 0115 530767/011 51573 37
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
