ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በ2018 በጀት ዓመት ኢአርፒ (ERP) ሲስተም ጥናት (ማልማት) ለማስጠናት አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የኢአርፒ (ERP) ሲስተም ጥናት (ማልማት) አገልግሎት ግዥ
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር NV/02/2018
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት በ2018 በጀት ዓመት ኢአርፒ (ERP) ሲስተም ጥናት (ማልማት) ለማስጠናት አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ሕጋዊ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች የዘመኑን የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በመንግስት የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ያላቸው የቫት ከፋይ የምስክር ወረቀት ያላቸው ስለመሆናቸው ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይመለያ ቁጥር /TIN ሠርተፍኬት፣በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ የመሳሰሉትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው መጀመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከኢንስቲትዩቱ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ወይም በራሳቸው ዋጋ ማቅረቢያ ፎርም መሰረት በመሙላት የድርጅታቸውን ማሕተምና ፊርማ በማድረግ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ /CPO/ ወይም /ቢድ ቦንድ/ የጠቅላላውን 2% በማስያዝ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኢንስቲትዩቱ ግዥ፤ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10፡30 ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ተዘግቶ 5:00 (አምስት ሰዓት) ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋም ሆነ በሌላ የጨረታ ጉዳይ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ንግድ ፍቃድ፤ ቲን ነምበር፤ ሲፒኦ የመሳሰሉት ከፋይናንሺያል ሰነድ ተለያይተው ለየብቻ በፖስታ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ፋይናንሽያልና ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኮፒ እና አንድ ኦሪጅናል ተለያይተው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- ቢሾፍቱ ከተማ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አለፍ ብሎ ከእንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ አጠገብ፣
ለበለጠ መረጃ ለማግኘት፡-
011-433-83-39 /09-12-22 99 01 መጠየቅ ይቻላል፡፡
ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት
