የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሎት አንድ ለተለያዩ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያላቸውን ባትሪዎች ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት እና በሎት ሁለት ደግሞ በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ሮለር እና ሎደር በድጋሚ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
የባትሪ ግዥ እና የማሽነሪ ደግሞ በድጋሚ ኪራይ አገልግሎት ለመፈፀም የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ደኢመባ ቁጥር 04/2018
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በሎት አንድ ለተለያዩ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያላቸውን ባትሪዎች ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት እና በሎት ሁለት ደግሞ በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ሮለር እና ሎደር በድጋሚ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ላለቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ሥለመሆናቸው ማስረጃ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግስት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ የቴክኒክ እና ፋይናንሻሉን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ለየብቻው በታሽገ ፖስታ የጨረታ ማስከበሪያው ደግሞ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለየ ፖስታ በማድረግ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በትክክል ማስፈር አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለየአንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና ቢሮ ቁጥር • መውሰድ ይችላሉ።
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል። ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች በእንግሊዘኛ የተጻፈውን የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ በሚጠይቀው መሠረት መሙላት ይጠበቅባቸዋል። ይህንን ያልሞሉት የቴክኒክ ዝርዝር መግለጫ እንዳልቀረበ ተቆጥሮ የማቅረብያ ሰነዱ ውድቅ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ለሎት ሁለት ለእያንዳንዱ ማሽን ብር 50.000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ እና ለሎት አንድ ደግሞ ከዚህ በታች በቀረበው መሠረት
|
ተ.ቁ
|
የዕቃው ዓይነት
|
Capacity (AH)
|
Qty
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
1
|
Lead-Acid Battery
|
70 Amp
|
20
|
5,000.00
|
|
2
|
Lead-Acid Battery
|
75 Amp
|
20
|
13,500.00
|
|
3
|
Lead-Acid Battery
|
210 Amp
|
14
|
1,200.00
|
|
4
|
Lead-Acid Battery
|
150 Amp
|
75
|
35,000.00
|
|
5
|
Lead-Acid Battery
|
120 Amp
|
08
|
3,500.00
|
|
6
|
Lead-Acid Battery
|
90 Amp
|
20
|
4,000.00
|
የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ/ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም ከኢንሹራስ ዋስትና በቀር በግዥ መመሪያው ላይ ባሉ አማራጮች በፈለጉት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ። ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳሉ፡፡ ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ለ45 ቀናት ፀንቶ መቆየት አለበት።
- ለሎት አንድ የጨረታው አሸናፊ ድርጅት መሆኑ ከተገለፀለት አምስት /5/ ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና /Performance Bond/ 10% በባንክ ጋራንቲ ወይም በሲፒኦ በማቅረብ ውል መፈረም ይኖርበታል፤ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ያልሆነ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል።
ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፦
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን
ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም
የፖሳቁ
የስልክ ቁጥር 046 131 5012/ 09 23 69 00 85
ፋክስ
ዲላ ኢትዮጵያ
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን
