Tender Detail

Tender Details

  • Company National Election Board of Ethiopia (የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ)
  • Address ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 115153468
  • Websitehttps://nebe.org.et/
  • Deadline12 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-12-12 00:00:00
  • Categories Other

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን እና ለምርጫ የሚውሉ ሚስጥራዊ ሰነዶችን ሚስጥራዊነታቸውን በጠበቀ መልኩ ፈጭተው መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ ፋብሪካዎች በሽያጭ በማስተላለፍ ለማስወገድ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን እና ለምርጫ የሚውሉ ሚስጥራዊ ሰነዶችን ሚስጥራዊነታቸውን በጠበቀ መልኩ ፈጭተው መልሰው ጥቅም ላይ ለሚያውሉ ፋብሪካዎች በሽያጭ በማስተላለፍ ለማስወገድ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት-

  1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ፋብሪካዎች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከመዘጋቱ በፊት ባሉ ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመፈል ከቦርዱ ንብረት አስተዳደር ፍል ቢሮ ቁጥር 506 ማግኘት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የመወዳደርያ ዋጋቸውን በጨረታ ሰነዱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብም ሆነ ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። በተጨማሪም አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀ የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የህትመት ውጤቶቹን የአንድ ኪሎ ነጠላ ዋጋ እና እንዲሁም በተጠቀሰው አጠቃላይ የክብደት መጠን ጠቅላላ ዋጋን በግልፅ በመሙላት ስም እና ፊርማቸውን ከታች ማስፈር አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ለጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ይሆን ዘንድ ብር: 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በባንከ የተረጋገጠ CPO በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  6. ጨረታው ታህሳስ 3 ቀን 2016 / 800 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 830 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦርዱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። በጨረታ ፈቻ ላይ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
  7. ተጫራቾች የራሳቸው የሆነ አገልግሎት የሰጡ ወረቀቶችን መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ፋብሪካ ያላቸው ሆነው ቦርዱ በሚያወጣውና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጡ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ሂደት የሚስማሙ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች በሽያጭ እንዲወገዱ የቀረቡትን የህትመት ውጤቶች እና የምርጫ ሚስጥራዊ ሰነዶች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከመዘጋቱ በፊት ባሉ ተከታታይ የስራ ቀናት ሳሪስ ቡና ቦርድ ፊት ለፊት በሚገኘው የቦርዱ ስልጠና ማዕከል እና መልካ ቃሊቲ ግቢ ባሉ መጋዘኖች በመገኘት በአካል መመልከት ይችላሉ።

 

ቦርዱ ሌላ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251115 51 02 52 ወይም ቦሌ መንገድ ከፍላሚጎ ገባ ብሎ ባለው የቦርዱ ዋና /መቤት 5 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 506 በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

 

Save Tender