Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤ/ጉ/ክልላዊ መንግስት መንገድና ትራስፖርት ቢሮ
  • Address , Phone: 0577752622
  • Website
  • Deadline20 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2025-12-20 00:00:00
  • Categories Construction Machinery , Construction Machinery And Vehicles

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት አመት ለሚሰሩ የመንገድ ስራ 4 ገልባጭ መኪናዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ ጨረታ ማስታወቀያ ቁጥር 04/2018

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ 2018 በጀት ዓመት ለሚያከናውናቸው ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ 4 ገልባጭ መኪናዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በበጀት ዓመቱ የንግድ ፈቃዳቸው የታደሠ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርያላችሁ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገባችሁ መሆናችሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. በመስኩ ሥራ ላይ ለመሰማራታቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሠነድ የያዘ ዶክመንት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ አሶሳበሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ///ዳሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  3. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት(አስራ አምስት ቀናት) አየር ላይ ቆይቶ 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾችወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ ዳሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
  4. የጨረታው መክፈቻ ቀን የህዝብ በዓላት ወይም ቅዳሜ እና አሁድ ላይ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው በታሽገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ የፋይናንስና የቴክኒክ ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ እና በማሸግ አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ//ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል ሠነዱን ይዞ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታው ማስከበሪያ ገንዘብ፤ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ በመ/ቤታችን ስም በተዘጋጀ CPO ብቻ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በፖስታ ለብቻው ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ (ጠቅላላ ዋጋ) ስርዝ ድልዝ እና በእርሳስ የተሞላ ሠነድ ተቀባይነት የለውም። የሚቀርበው ዋጋ 5% ቫት ጋር ወይምከ5% ቫት በፊት ተብሎ በግልጽ ተጽፎ መቀመጥ አለበት ይህ ካልሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴትታክስ እና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ሰርተፊኬት ኮፒውን ይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. የገልባጭ መኪናዎች መረካከቢያ ቦታ አዲስ አበባ ሆኖ በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ገልባጭ መኪናዎቹ በመጋዝን /በሰቶክ/ ለመኖራቸው ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አሽናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  11. /ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር - 0577752622/0911130761 ዘወትር በሥራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

የቤ//ክልላዊ መንግስት መንገድና ትራስፖርት ቢሮ

Save Tender