Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ቴሌኮም
  • Address addis ababa, Phone: 00 00 00 00
  • Websitehttp://www.ethiotelecom.et
  • Deadline12 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening date2025-12-12 00:00:00
  • Categories Ict And Telecom Service , Equipment

ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SC/L/WRM/002/2018

 

ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የእጅ ሞባይሎች ቀፎዎች፤ የቤት ስልኮች እና ሞደሞች፣ የፓወር እና ኔትዎርክ ስፔር ፓርቶች፣ የፊክስድ ኔትዎርክ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ዐይነት ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር ሲፒዩ እና ሞኒተሮች፣ የተለያዩ  ዓይነት ራኮች፣ የኔትዎርክ አንቴናዎች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ፕሪንተሮች፣ ፋክስ ማሽኖች፤ ሲግኒቸር ፓዶች፤ ስካነሮች እና የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች፣ ያገለገሉ ላፕቶፖች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ስፔር ፓርቶች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ሰርቨሮች፣ የተለያዩ የአይሲቲ ስፔር ፓርቶች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ስክራኘ የፖል እንጨቶች፣ ብረታብረቶችንና ራኮችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 20 ቀን 2018 . እስከ ታህሳስ 03 ቀን 2018 . ከቀኑ 1100 ድረስ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት ከኦክሽን ኢትዮጵያ ዌብ ሳይት ወይም ከኦክሽን ኢትዮጰያ መተግበሪያ በመግባት ማግኘት እና መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ንብረቶቹን  መመልከት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ተጫራቾች  አቃቂ  በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ግምጃ ቤት በወሎ ሰፈር በሚገኘው የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤቶች እንዲሁም በምስራቅ አዲስ አበባ (ገርጂ) በሰሜን አዲስ አበባ (ፈረንሳይ) እና በምዕራብ አዲስ አበባ (አስኮ) በመገኘት የታደሰ መታወቂያችሁን በመያዝ መጎብኘትና መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብ መወዳደር ይችላሉ።

የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ በኦክሽን ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል 9164/ 090511-5511 ወይም 0116-66-8828 ደውሎ መረዳት ይቻላል።

ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ኢትዮ ቴሌኮም

Save Tender