Tender Detail

Tender Details

  • Company በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት
  • Address ጌዴኦ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461310108
  • Website
  • Deadline31 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2025-12-31 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Soil Fertilization

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙት ለቡሌ እና ለራጴ ወረዳ አሲዳማ አፈርን ለማሻሻል አገልግሎት የሚውል የአፈር ኖራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ የአፈር የኖራ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ግብርና መምሪያ 2018 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙት ለቡሌ እና ለራጴ ወረዳ አሲዳማ አፈርን ለማሻሻል አገልግሎት የሚውል የአፈር ኖራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

  • በበጀት ዓመቱ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • በግብርና ሚኒስቴር የጥራት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶችን የሚያሚሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 200 / ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ሰነዱን ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፤ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 60,000 /ስልሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚሸጡበትን የኖራ ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
  • ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት፣
  • በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤
  • ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 15 ቀናት በኋላ 16ኛው ቀን የጨረታው ሳጥን ጠዋት 400 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 230 እስከ 400 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
  • የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት ነው፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉትን ኖራ ጌዴኦ ዞን ቡሌ ወረዳ ኢላቻ ቀበሌ እና ራጴ ወረዳ ሃሮ ወላቦ ቀበሌ ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የአውራጅ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-131-01-08 መደወል ይችላሉ።

በጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት - ዲላ

Save Tender