በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ የአየር ንብረት አፈጻጸም የመሬት አያያዘ ፕሮግራም /CALM /አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የደን ችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 10 ሎት 02 የአትክልትና ፍራፍሬ ቡና ችግኝ ማፍያ ባለ 14 እና ባለ 20 ሚሜ እና ሎት ዐ3 የውሃ ማጠጫ ጀርዲን ግዥ በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ቁጥር 05 በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ የአየር ንብረት አፈጻጸም የመሬት አያያዘ ፕሮግራም /CALM /አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የደን ችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 10 ሎት 02 የአትክልትና ፍራፍሬ ቡና ችግኝ ማፍያ ባለ 14 እና ባለ 20 ሚሜ እና ሎት ዐ3 የውሃ ማጠጫ ጀርዲን ግዥ በግልጽ ጫረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደርየሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሱ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ፤
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕለስቲከ ጆርዲን እና የዕጅ ጋሪ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺ ብር በመከፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁርጥ ለሎት 01 ብር 300,000.00 /ሶስት መቶ ሺ ብር/ ሎት 02 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር እንዲሁም ለሎት 03 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ( Unconditonal Bank Guarantee)ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ/መወዳዳሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴከኒካል ሰነዱ ጋር አብረው መቅረብ አለባቸው፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16ኛ ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
10. በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582205849/0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይቻላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡
12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ
