Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት
  • Address ትራፊክ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ስድስተኛ /6/ ፎቅ ቢሮ ቁ 6-03 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-6-67-44-30
  • Website
  • Deadline29 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-12-29 00:00:00
  • Categories Office Machines And Accessories , Office Equipment

የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ጽ/ቤቱ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ አይነት ዴስክቶፕ፣ ፕሪንተር, ፎቶኮፒ ማሽን፣ ብረታብረት፣ ምንጣፍ፣ የቢሮ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ሌዘር ሶፋዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- /////_01/2018

 

የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት /ቤቱ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ አይነት ዴስክቶፕ፣ ፕሪንተር, ፎቶኮፒ ማሽን፣ ብረታብረት፣ ምንጣፍ፣ የቢሮ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ሌዘር ሶፋዎች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ማንኛውም ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ አካል ንብረቶቹ ያሉበትን ሁኔታ ሃያሁለት በሚገኘው ትራፊክ /ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መመልከት ይችላሉ።

  • ማንኛውም ተጫራች ከአንድ በላይ እቃዎችን ለመግዛት መጫረት ይችላል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከጽ/ቤቱ 6 ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ያንዱ ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚገዙበትን የአንዱን ዋጋ እንዲሁም ጠቅላላ ዋጋውን በማብዛት ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ /ቤት ስድስተኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  • ማንኛውም ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በመለየት ዋጋቸውን ጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ በመሙላት እና በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  • ተጫራቾች ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  • ከጨረታ ሰነዱ ውጪ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
  • ጨረታው ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ቀናት አየር ላይ ይውልና 11ኛው ቀን 400 ታሽጎ በዚሁ ቀን 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ 2 ፎቅ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ሲሆን በጨረታ አከፋፈት ስነ ስርዓቱ ላይ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግድም።
  • ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ሙሉ ክፍያ 2 ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ንብረቱን በአንድ ሳምንት ጊዜ ማንሳት አለባቸው። ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ያስያዙት ሲፒኦ ለጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ሁለተኛ ለወጣው ተጫራች ይተላለፋል።
  1. የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
  2. አንዱ ድርጅት በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  3. /ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116-674430 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ ሃያ ሁለት ትራፊክ /ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት

Save Tender