Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የቤንች ማጂ አንድነት የገ/ሁ/ህ/ስራ ዩኒዬን
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline02 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-01-02 00:00:00
  • Categories Soil Fertilization

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በቤንች ማጂ አንድነት የገ/ሁ/ህ/ስራ ዩኒዬን በ2018 በጀት ዓመት ለአርሶ አደሩ ምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አይነት ያላቸው የአፈር ማዳበሪያ ከቤ/ሸኮ ዞን ማእከላዊ መጋዘን በዞኑ ለሚገኙ ወረዳዎችና በሸካ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች ለማጓጓዝ ስላቀደ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለማሰራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በቤንች ማጂ አንድነት የገ///ስራ ዩኒዬን 2018 በጀት ዓመት ለአርሶ አደሩ ምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አይነት ያላቸው የአፈር ማዳበሪያ ከቤ/ሸኮ ዞን ማእከላዊ መጋዘን በዞኑ ለሚገኙ ወረዳዎችና በሸካ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች ለማጓጓዝ ስላቀደ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለማሰራት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ያላቸው።
  3. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  4. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ከመንገድ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል።
  5. የባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ የሚችል።
  6. የታደሰ መድን ሽፋን ወይም መድን ፈንድ ማቅረብ የሚችል።
  7. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ የሚችል።
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከቤ/ሸኮ ዞን የቤንች ማጂ አንድነት የገ/// ስራ ዩኒዬን ቢሮ .2 በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ፋይናሻልና ቴክኒካልን ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾችን ህጋዊ ውክልና፤ ፊርማ፤ የድርጅቱን ማህተም፣ ፋይናሻልና ቴክኒካል፣ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት ፖስታው ላይ በመጻፍ እንዲሁም አድራሻና ስልክ መግለጽ መቻል አለባቸው።
  11. የትራንስፖርት የመጫን አቅም 100 (አንድ መቶ ኩንታል እና ከዚያ በላይ
  12. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን 15ኛው በቤ// የገ/// ስራ ዩኒዬን ቢሮ ከጠዋቱ 400 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ጨረታው የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ከመንግስት ስራ ሰዓት ውጭ/በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ/በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የቤንች ማጂ አንድነት የገ///ስራ ዩኒዬን

 

Save Tender