የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት አስመጪዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈፅመው ባለመውሰዳቸው የተተዉና የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የተለያዩ የConstraction Equipment and Materials የተለያዩ ዓይነት ጀኔሬተሮች እና ሁለት Truck with Crane Truck with Crane በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 19/2018
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት አስመጪዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈፅመው ባለመውሰዳቸው የተተውና የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የተለያዩ የConstraction Equipment and Materials የተለያዩ ዓይነት ጀኔሬተሮች እና ሁለት Truck with Crane Truck with Crane በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከፍተኛ የመሸጫ ዋጋው ከብር 500 መቶ ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላከልዎት ማድረግ ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O በማሠራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 7ኛው (ሰባተኛው)ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ8ኛው (በስምንተኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ የውርስ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል /እሁድ/ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለው የሥራ ቀናት ከላይ በተገለፀው ቦታ እና ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ባቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸው። ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም ። በተጨማሪ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
- ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
- አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96/ 046-212-65-95
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
