የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት ውስጥ ለሚገኙት የሕግ ታራሚዎች ለምግብ አቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል፣ ማጣፈጫ እና የማገዶ እንጨት ለ2018 ዓ.ም በጀት ለሁለተኛ ዙር ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ለ 6 (ስድስት) ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ለአንደኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት ውስጥ ለሚገኙት የሕግ ታራሚዎች ለምግብ አቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል፣ ማጣፈጫ እና የማገዶ እንጨት ለ2018 ዓ.ም በጀት ለሁለተኛ ዙር ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ለ 6 (ስድስት) ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ማንኛውም በጨረታ ውል መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ
- የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም ቢሮ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና አግባብነት ያለው የ2018 የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተመዘገቡ ወይም የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 (ሠላሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዞኑ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞን ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት ከመቶ (2%) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) እና የምግብ እህል ናሙና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ተደራጅቶ የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማኅበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ካልተገኘ በጥሬ እህል እናወዳድራለን፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በሥራ ቀን ከረፋዱ በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ያስገቡበት ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት በዞኑ ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሕግ ታራሚ ኮሚቴዎች እና የማረሚያ ቤቱ ሠረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የዞኑ ማረሚያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀ ማብሰያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስሎ ማቅረብ የሚችል
ማረሚያ ቤቱ የሚገኝበት ከተማ
|
ተ.ቁ |
የዞን ማረሚያ ቤት |
የሚገኙበት ከተማ |
|
1 |
የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት |
ጊንር |
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 0911645276 /0911803891 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የምሥራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት
