Tender Detail

Tender Details

  • Company የሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን ኃ/የተወሰነ
  • Address ሆለታ ከተማ ግብርና ምርምር በሚወስደው መንገድ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-237-09-71
  • Website
  • Deadline01 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price2000.00
  • opening date2026-01-01 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Chemicals And Reagents , Pharmaceutical Products

ሮቢ በርጋ የ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን በመጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ጊዜ ያለፈባቸው ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ ለሦስተኛ ጊዜ እና የተለያዩ ፀረ አረም እና የዋግ መድኃኒት ለሁለተኛ ጊዜ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ እና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የተለያዩ ፀረ አረም እና የዋግ መድኃኒት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ሮቢ በርጋ //ሥራ ዩኒዬን በመጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ጊዜ ያለፈባቸው ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ ለሦስተኛ ጊዜ እና የተለያዩ ፀረ አረም እና የዋግ መድኃኒት ለሁለተኛ ጊዜ በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ በተወሰነው መሰረት፣ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶቹም፤

  1. ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ (Expired) እና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ፀረ አረምና የዋማ ኬሚካል የስራ ፍቃድ ያለው እና 2018 . የታደሰ ሥራ ፈቃድ፣ TIN, ግብር ስለመፈል የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. ተጫራቾች ይህንን ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደር እንደማያቀርቡ እና አቅርበው የሚገኙ ከሆነ በሕግ ስለመጠየታቸው የሚያስረዳ ደብዳቤ ለሮቢ በርጋ የነበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩንዬን ማቅረብ የሚችል፤
  3. ተጫራ ጠቅላላ የተወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 8% CPO በኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ እና ንግድ ባን በሮቢ በርጋ የነበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩንዬን ስም ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን፣ የጨረታው ማስከበሪያ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ሲመለስ፤ ለአሸናፊዎች ግን ሥራውን በተዋዋሉት መሠረት ሲያጠናቅቁ አፈፃፀማቸው ታይቶ እና ተረጋግጦ የሚመለስላቸው ይሆናል።
  4. ተጫራቾች በዩንዬኑ መጋዘን በአካል በመገኘት የምርት ግብዓቶቹ ያሉበትን ሁኔታ በማየት የተዘጋጀውን ሰነድ በብር 2,000 በመግዛት፤ ለእያንዳንዱ ለሚገዙት ግብዓት የሚገዙበትን የአንድ ኩንታል እና ሊትር ዋጋ በብር መስጠት አለባቸው፤
  5. ተጫራቾች/ተወካዮቻቸው በጨረታው ፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፊት ወይም ባይገኙም ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7ኛው ቀን ከቀኑ 400 ታሽጎ በዚሁ እለት 405 ሰዓት ጠዋት በዩኒዬኑ ቢሮ ይከፈታል። 7ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  7. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
  8. ተጫራቶች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በአምስት ቀን ውስጥ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈርማዳበሪያ እና ፀረ አረምና የዋግ መድኃኒት በዩንዬኑ መጋዘን ውስጥ ተሰብስቦ የሚገኘውን በመለየት በወቅቱ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የሚረከብ ይሆናል።
  9. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎችን ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመለየት በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማሕተም፣ ስም እና ፊርማ ተደርጎበት መቅረብ አለበት፡፡
  10. ዩኒዬኑ በጨረታው ላይ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ሮቢ በርጋ የገ//ሥራ ዩኒዬን ሆለታ ከተማ ግብርና ምርምር በሚወስደው መንገድ

ስልክ ቁጥር፡- 09-13-92-79-93/0913-07-10-00

 

የሮቢ በርጋ የገ//ሥራ ዩኒዬን

Save Tender