Tender Detail

Tender Details

  • Company የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
  • Address , Phone: 0461800863
  • Website
  • Deadline17 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-01-17 00:00:00
  • Categories Stationery Materials , Equipment

በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችንና እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

  1. በደቡብ ኢት/ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችንና እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1- የጽህፈት መሳሪያ - ሎት 15 የሞተር ሳይክል ጥገና ስሶስተኛ ጊዜ የወጣ ሎት 17- የእንስሳት መድሃኒት ሎት18- ለህጻናት ማቆያ የሚሆነ የምግብ ዓይነቶች፣ ሎት 19- የማባዣ ማሽን ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ -

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉት በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና 2018 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና eGP የተመዘገቡ፣ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ ሥራዎች አገልግሎቶች ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል።
  4. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 400 (አራት ሰዓት) ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 430 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ፡- ሎት 1 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለሎት- 15 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለሎት- 17 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ለሎት- 18- 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለሎት-19 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ርክብክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል፡፡
  8. የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 046 180 0863 ደዉሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ

Save Tender