Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል
  • Address ከሚሴ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 51 99 99 75
  • Website
  • Deadline15 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceየማይመለስ የኢትዮ.ብር 500/አምስት መቶ ብር ብቻ
  • opening date4፡30 ሰዓት
  • Categories Office Supplies And Services , Stationery Materials , Vehicle Spare Parts

በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ፣የፅህፈት መሳሪዎች የመኪና መለዋወጫ እና ጌጣጌጦች እቃዎች፣የፅዳት እቃዎች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፡-


የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል 2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ፣የፅህፈት መሳሪዎች የመኪና መለዋወጫ እና ጌጣጌጦች እቃዎች፣የፅዳት እቃዎች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፡-

1.     በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ /IN/ያላቸው፡፡

2.     የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 50 በግዥ//ንብ/አስ/የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ከላይየተዘረዘሩትን መረጃዎች ዘውትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ.ብር 500/አምስት መቶ ብር ብቻ /በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

3.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ ከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስተኛዉ/16/ቀን ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ 400 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4.     ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን 401 ሰዓት ተዘግቶ 430 ሰዓት ላይ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡የመከፈቻ እለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡

5.     ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ2% /ከሁለት ፐርሰንት/በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንከ ትእዛዝ/CPO/ማስያዝ አለባቸው::

6.     የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

7.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8.     የዕቃው ርክክብ ቦታ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ይሆናል፡፡

9.     ውድድሩ በነጠላ ዋጋ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

10.                        ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር +251972847872 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡

በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of office supplies, stationery, vehicle spare parts, decorations, cleaning items, and uniforms for Kemissie General Hospital. Bidders must hold valid trade license, registration certificate, and tax ID. Delivery at the hospital.
Save Tender