ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅ/ስራ ዩኒየን በያዝነው 2018/19 ምርት ዘመን ከሃዋሳ ማእከል የበልግና መኸርየአፈር ማዳበሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቶች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መግለጫ ሰነድ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅ/ስራ ዩኒየን በያዝነው 2018/19 ምርት ዘመን ከሃዋሳ ማእከል የበልግና መኸርየአፈር ማዳበሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቶች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መግለጫ ሰነድ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፈቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፡፡
2. ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
3. ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ ተሰማርቶ በአንድ ጊዜ ኮንትራት ውል 50000 ኩንታል በላይ በማንጓዝ ስራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ስራ አፈፃፀም ቢያንስ ሶስት ማቅረብ የሚችል።
4. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር ያመች ዘንድ በአንድ አከባቢ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደርአይችሉም።
5.ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፉበትን ጭነት የማጓጓዣ ዋጋ 10 % በቅድሚያ ያስይዛል፡፡
7. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 2000/ሁለት ሺህ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን የሰሌዳ ቁጥር የሻንሲ ቁጥር የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አይይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ለሚጠፋው ንብረት በሙሉ ሃላፊነት የሚወስድ የጭነት ኢንሹራንስ ካርጎ ኢንሹራንስ ያለውና መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 300.00 ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7/ሰባት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይየሚውል ይሆናል።
11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴከኒካል ዶክመንት 1 ኦሪጅናልና 1 ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶክመንት አሪጅናል 1 እና ኮፒ ለየብቻው ሆኖ በአንድ እናት ካኪ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
12. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ8ኛው ቀን የጨረታ ሰነዳቸውን በመሙላት ለዚህ ተበሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ ቀኑ 9፡30 የሚያስገቡና ከቀኑ 10፡00 ታሽጎ በ10፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የጨረታ ተሳታፊዎች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ለበለጠ መረጃ ፡- ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመቅረብ አልያም በስ.ቁ 046-212-4704 በመደወል
መረጃ ማግኘት ይችሳሱ፡፡
ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተ.
