የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንገዶች ባለስልጣን ለቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ መለዋወጫዎች በሎት-1- የቀላል ተሸከርካሪዎች መለዋወጫ /light Duty Vehicles spare parts /LDV/፣ በሎት- 2 - የከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ /Heavy Duty Vehicles spare parts /HDV/ እና በሎት-3 - የከባድ ማሽነሪዎች መለዋወጫ /Earth
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ማ/ኢ/መ/ባ/-SP-04/18
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንገዶች ባለስልጣን ለቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ መለዋወጫዎች በሎት-1- የቀላል ተሸከርካሪዎች መለዋወጫ /light Duty Vehicles spare parts /LDV/፣ በሎት- 2 - የከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ /Heavy Duty Vehicles spare parts /HDV/ እና በሎት-3 - የከባድ ማሽነሪዎች መለዋወጫ /Earth Moving Equipment's spare parts /EME/ ብቁ ተጫራቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ, የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ መንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች በታሽገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ዋና እና ሁለት ኮፒ የቴክኒካል ፕሮፖዛሉን ዋና እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በየሎቱ በተለየ ፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ/ ብር ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈረቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተመሰሳይ ሠዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዘንድ ዕውቅና ካላቸው የፋይናንስ ተቋም በቅደመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ሲ ፒ ኦ /c.p.o/ ለአንድ ሎት ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በኢንሹራንስ ዋስትና የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም
የስልክ ቁጥር 0113659932
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን
ወልቂጤ ኢትዮጵያ
