በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለክሊንከር ምርት ጥሬ እቃ ማቃጠያ የኃይል ምንጭ አገልግሎት የሚጠቀምበት 75,000 (ሰባ አምስት ሺህ) ሜ.ቶን የሀገር ውስጥ የታጠበ ድንጋይ ከሰል (Local Washed Coal) አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀገር ውስጥ ጨረታ ቁጥር
ሚሲፋ/Re-02/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለክሊንከር ምርት ጥሬ እቃ ማቃጠያ የኃይል ምንጭ አገልግሎት የሚጠቀምበት 75,000 (ሰባ አምስት ሺህ) ሜ.ቶን የሀገር ውስጥ የታጠበ ድንጋይ ከሰል (Local Washed Coal) አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ህጋዊ የንግድ ምዝገባና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብርየከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታከስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ 575.00 (አምስት መቶ ሰባ አምስት ብር) ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በመከፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት ጋራድ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ _ኮርፖሬሽን _ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼከ (C.P.O.) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴከኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በግዥ መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በእለቱ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ከዓት በግዥ ምምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ:0114420216
ፋክስ፡ 0114420688
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ