በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ብዛታቸው 15 /አስራ አምስት/ የሚሆኑ CCTV Camera ለማስገጠም በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ድጋሚ የጨረታ ቁጥር ኬኢኮአመኬፋ 004/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ብዛታቸው 15 /አስራ አምስት/ የሚሆኑ CCTV Camera ለማስገጠም በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም-
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
2. የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀትን ታክስ ክሊራንስ፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገቡን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የስራ ቀናት አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንፃ ውስጥ ከአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ የማይመለስ ብር 300 /ሁለት መቶ/ በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ ከ2% ያላነሰ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ቼክ ወይም በባንኮች የተረጋገጠ ጋራንቲ ደብዳቤ ከ90 ቀን ያላነሰ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
5. ቴክኒካል አፈርና ፋይናንሺያል አፈር ኦሪጅናልና ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ ታሽገው ቴክኒካል አፈር፣ ፋይናንሺያል ኦፈር ተብሎ ተፅፎበት እስከ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በፊት ከአዳማ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ጨረታው ዓርብ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ቴክኒካል ኦፈሩ ብቻ በዕለቱ ዓርብ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ዋናው መ/ቤት ይከፈታል፡፡
7. ፋይናንሽያል ኦፈሩ ዓርብ የካቲት 20 ቀን 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ዋናው መ/ቤት ይከፈታል፡፡
8. ድርጅቱ/ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 022 225 0266/022 225 0750
ሞባይል 0920935336/0987960770
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ
