የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል ነጭ በቆሎ በጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ወማተ/ጨ1/1430/18
የወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ5 ወራት በሚቆይ የአቅርቦት ጊዜ ሆኖ በአቅራቢና ተቀባይ መካከል በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት አምስት ወራት ለሚደርስ የግዥ ዘዴ በየወሩ ለሚያቀርቡ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
|
ተ.ቁ
|
የአቅርቦቱ አይነት
|
መለኪያ
|
የአቅርቦት መጠን
|
የማቅረቢያ ጊዜ
|
ርክክቡ የሚፈፀሚበት ቦታ
|
በቅድሚያ ለ03 ወራት ቆይታ ጊዜ ከ_እስከ
|
|
01
|
ነጭ በቆሎ
|
በኩ/ል
|
ከ600-700 ኩንታል
|
ወር በገባ ከ25-30 ድረስ
|
ተቋሙ ቅጥር ግቢ
|
ከ1/06/2018- 30/10/2018
|
መመዘኛዎች
(01) በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ላት/ የዘመኑን ግብር የከፈለ/ች/፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ ላት/፤ ከማንኛውም ግብርና ታክስ ከፋይነት ነፃ እንዲሆኑ ከተፈቀደላቸው ድርጅቶችና ዩኒየኖችና ተመሳሳይ የንግድ ድርጅቶች በስተቀር የVAT 15% ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸው፤
(02) ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አቅርቦት በቀደምት የሥራ ዘመን ተጫርተው በማሸነፍ ለማረሚያ ተቋማት ወይንም ለሌሎች መንግስታዊና ሕዝባዊ ድርጅቶች ለ01 (አንድ) ዓመት እና ከዚያም በላይ ለሆነ ጊዜያት ያለ እንከን ስለማቅረባቸው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ደብዳቤ /ምስክር ወረቀት/ ማስረጃ ከሌሎች መጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
(03) አሸናፊው ተጫራች ለአቅርቦቱ ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሠረት ከየካቲት 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ወራቶች በየወሩ ለማቅረብ ህጋዊ የውል ሰነድ የሚፈርምና ያሸነፈው ነጠላ ዋጋ እንደተጠበቀ ሆኖ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሚሆን ፣
(04) ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/ደ/ሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን፤ የጨረታ ማስከበሪያን በሚመለከት ከጠቅላላ አቅርቦት ዋጋ 2% የብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ CPO/ተመሳሳይ/ ሰነድ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
(05) ተጫራቾች፡- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር / ተከታታይ ቀናት የበቆሎውን የአንዱን ኩንታል ነጠላ ዋጋ በመሙላት ከነማስረጃው ኮፒዎች ጋር በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አዘጋጅተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
(06) ተጫራቾች የበቆሎውን ናሙና የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም
(07) ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች /ህጋዊ/ወኪሎቻቸው በተገኙበት 11ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት በማረሚያ ተቋሙ ቅጥር ግቢ አዳራሽ /ቢሮ/ የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ ዕለቱ የበዓላት /የዕረፍት/ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እያሳሰብን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- 011-330-0154፡ 011-330 1139: 011-330-1568 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
ወልቂጤ ማ/ተቋም
