የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የጥበቃ አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመፈጸም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 31/2018
1. የጥበቃ አገልግሎት ግዥ
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- ቫት ተመዝጋቢ
- ታክስ ክሊራንስ
- በግዥ ባለስልጣን የምዝገባ ማስረጃ
- የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት
- በዘርፉ የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ወረቀት
· ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ 30 (ሰላሳ) ቀናት
· የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ) ብር ሆኖ የጨረታ ማስከበሪያው በሲ.ፒ.ኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መሆን ይኖርበታል፡፡
· ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ሰነዱ በሚገኝበት በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት በግዥ ክፍል ቢሮ, ቁጥር 01 የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
· የጨረታ ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን እና ሰዓት 03/06/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት
· ጨረታው የሚከፈተው፡- በዕለቱ 03/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
· ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
· ለበለጠ መረጃ እና ማብራሪያ ዋናው መስሪያ ቤት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 0114171703 መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡-
· የኢትዮጵያ የከፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ (ዋና መስሪያ ቤት ቱሉ ዲምቱ)
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
