ኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር ለህንፃው አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ያገለገለ 1 (አንድ) ትልቅ ጀኔሬተር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ያገለገለ ጀኔሬተር ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ
ኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር ለህንፃው አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ያገለገለ 1 (አንድ) ትልቅ ጀኔሬተር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
1. በዘርፉ 2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣
2. የቫት እና የግብር ከፋይነት ሰርቲፈኬት (TIN Number)
3. ለሚከፈለው ክፍያ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፣
4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ 5,000 ባንክ ሲፒኦ (CPO) አሰርቶ በማህበሩ ስም ማስያዝ የሚችል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች የሚያሟሉ ተቋራጮች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 (በአስር) የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ከአክሲዮን ማህበሩ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሞሎትን የመጫረቻ ዋጋቸውንና አስፈላጊ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
5. ጨረታው ከወጣበት ቀን አስረኛው ቀን 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዛው ቀን 9፡00 ሰእት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአከሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን አ/ማህበሩ ለተወዳዳሪዎች በስልክ ያሳውቃል፡፡
6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ3 (ሶስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን በመረከብ ካለበት ማንሳት ይኖርበታል፡፡
7. ለእቃው ማስነሻና ማጓጓዣ ወጪ በአሸናፊው የሚሸፈን መሆኑን መታወቅ ይኖርበታል።
8. አሸናፊ ተጫራች ንብረቱን ተረከቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለአ/ማህበሩ ገቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ በጨረታ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
· ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
· አድራሻች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው አጠና ተራ ከቴሌው ጀርባ ባለው የአ/ማህበሩ የገበያ ማዕከል ሕንጻ ቁጥር 2 አራተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 4
· ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-12-05-47-92 /09-32-08-03-77
ኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር
