በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል እቃ እና አገልግሎት - ሎት 1 እስቴሽነሪ 1፣ ሎት2 የግንባታ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4. የዶሮ መኖ፣ ሎት 5 የእንቁላል ጣይ ዶሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል እቃ እና አገልግሎት - ሎት 1 እስቴሽነሪ 1፣ ሎት 2 የግንባታ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4. የዶሮ መኖ፣ ሎት 5 የእንቁላል ጣይ ዶሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
4. የሚሞሉት ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ለእስቴሽነሪ 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ/፣ ለግንባታ እቃዎች 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/፣ ለፅዳት ዕቃዎች 2,000 /ሁለት ሺህ ብር ብቻ/፣ ለዶሮ መኖ 6,000 /ስድስት ሺህ ብር ብቻ/ ለእንቁላል ጣይ ዶሮ 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና /ኦርጂናል እና ቅጂ ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 17/06/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀላፊ ክፍል በቢሮ ቁጥር 1 በ 17/06/2018 ዓ/ም ጠዋት 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
11. ተጫራቹ የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ በማሟላት ዕቃው የተመረተበትን አገር፣ የአምራቹን ስም፣ የዕቃውን ሞዴልና የመሳሰሉትን አካቶ መሙላት ይጠበቅበታል፡፡
12. ውድድሩ በሎት ድምር ዋጋ ወይም በነጠላ ዋጋ ሊሆን ይችላል፡፡
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0224720080 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
