የደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡002/2018
የደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ማለትም ፡-
የደንብ ልብሶች
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
ልዩ ልዩ መሣርያዎች
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-
1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት : ተመዝግበው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4.ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5.ተጫራቾች ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥርነo ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
6.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረብያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም ፤ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ 2፡30-11፡00 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
7.ለጨረታ ማስከበርያ ሎት 1) 5884.76 ሎት 2) 22167.98 ሎት 3) 19559.56 ሎት 4)21058.04 ሎት
5) 217850.17 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበርያ ማስያዝ ይኖርቦታል፡፡
10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበርያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው፡፡
11. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘ ቀን ከጠዋቱ 4፡ oo ተዘግቶ ቀን ከቀኑ በ5፡00 ሰዓት በትምህርት ቤቱ የግ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር10 ይከፈታል፡፡
12. መስርያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0114343278/ 0114715349
14. ጥቃቅንና አነስተኛ በሃገር ውስጥ ምርት ላይ የተሳተፉ ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ገዝተው እና CPO አስይዘው መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፦ በአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ከቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ ከአሮጌው አስፓልት 200 ሜትር ገባ ብሎ
የደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
