Tender Detail

Tender Details


በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሰራተኞች ደንብ ልብስ

አላቂ የቢሮ እና የትምህርት እቃዎች

የህከምና እቃዎች

ቋሚ የቢሮ እቃዎች

የላብራቶሪ እቃዎች

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

1. በመስኩ አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት መረጃ ያላቸው::

4.ጥራት ያለው ዕቃ ማቅረብ የሚችሉና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የዕቃዎቹን ናሙና በፎቶ አስቀድሞ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5.የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 10,000.00/ አስር ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ/CPO/ ማስያዝ የሚችሉ፡፡

6.ለጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዢ እና ፋይናንስ ከፍል መግዛት ይችላሉ፡፡

7.ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ስም ክብ ማህተም እና ፊርማ በታሸገ ኢንቨሎፕ ዉስጥ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት በገዙት ዝርዝር ሰነድ ላይ በግልፅ መፃፍ አለባቸው ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ፊርማውን ከአጠገቡ ማሰቀመጥ ግዴታ አለበት ፡፡

9.ጨረታው ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በ11 ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በምክትል ርዕሰ መምህር ቢሮ ይከፈታል፡፡

10.ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱን ዋጋ የሞላውን በጠቅላላ ድምር ላይ ማሰቀመጥ የጠበቅበታል፡፡

11.ተጫራቹ የሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ቼከ/CPO/ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡

 

12 ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ - ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከታከሲ ማዞሪያ ከፍ ብሎ የካ ኢንዱስትሪያ ኮሌጅ ፊት ለፊት የሚገኘው ህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

ስ.ቁ 01111400 80 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

P.o box 20055

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ትምህርት ጽ/ቤት የህዝባዊ ሰራዊት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መለስተኛ ሁስተኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender