የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሚከተሉትን የማሽነሪዎች እና የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ከዚህ በታች በሎት ተከፍሎ በተቀመጠው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ከ6 ወር ያላነሰ ጊዜ ውል ፈፅሞ ለመስራት ፍላጎት ካለው ድርጅት ጋር የኪራይ አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የኮንስትራክሽን ማሽነሪ እና የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ኪራይ
አገልግሎት ግዥ በድጋሚ የወጣ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ 09/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሚከተሉትን የማሽነሪዎች እና የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን ከዚህ በታች በሎት ተከፍሎ በተቀመጠው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ከ6 ወር ያላነሰ ጊዜ ውል ፈፅሞ ለመስራት ፍላጎት ካለው ድርጅት ጋር የኪራይ አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ሎት፡- የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኪራይ እና ሎት 2፡- የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ኪራይ (ከባድ መኪና አይሱዚ እና pick up መኪና)
ስለሆነም
1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ኮፒ /ክሊራንስ ኮፒ/ ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን እና በአቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማስልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና ለሎት 2 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ
ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 09-20-11-75-60
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት
