በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት የፋብሪካ ውጤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት፡- የፋብሪካ ውጤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
የግብር መለያ Tin ቁጥር ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ፣ በCpo ፣ በጥሬ ገንዘብ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ከ 1 እስከ 5 የተጠቀሰውን ማስረጃዎችን እና የማጫረቻ ሠነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ውስጥ በማስገባት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ፣ እሁድ እና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በመንግስት ሥራ ሰዓት ይከፈታል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሣውላ ማረሚያ ተቋም የግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ ጨረታ የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን በራሳቸው ወጪ እስከ ሣውላ ማረሚያ ተቋም አምጥተው ማስረከብ አለባቸው፡፡
የጨረታው አሸናፊዎች ሆነው የተገኙ ተጫራቾች የዕቃዎችን አጠቃላይ ዋጋ በ10% በባንከ የተረጋገጠ ቼክ ወይም /CPO/ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሳውላ ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደ/ሥራ ሂደት ጋር የውል ስምምነት መፈፀም ይጠበቅባቸዋል፡፡ በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መወዳደር ተቀባይነት የለውም፡፡
ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡- 0916877379/0916479909
የሣውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም
