በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ያስገነባው የጋራ መኖርያ ቤት ቃሊቲ ሁለት (2) ተብሎ የሚጠራው ሳይት አጠገብ ባለ G+3 ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር መ.ሠ.ፋ/ብ.ግ. ጨ-016/2018
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ያስገነባው የጋራ መኖርያ ቤት ቃሊቲ ሁለት (2) ተብሎ የሚጠራው ሳይት አጠገብ ባለ G+3 ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ህንፃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ለተለያየ አገልግሎት የሚውል ባለ G+3 ሕንጻ ኪራይ
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ የምትሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ተጫራቾች ሊከራዩ በፈለጉት ቤት በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ /VAT/ Registration Certificate/፤ እና የቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መ.ሰ.ፋ ግዥ ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 015 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማለትም የወሩን የኪራይ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሃያ በመቶ (20%) ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ስም አሰርተው በመስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ ተለይቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቢሮ ቁጥር 015 በመምጣት መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
5. ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ልክ4፡00 ሰአት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 መ.ሰ.ፋ ግዥ ቡድን ይከፈታል።
6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው እና የውል ስምምነት የሚፈፅሙ ይሆናል።
7. በጨረታ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
8. ፋውንዴሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው ሳንድ ማርክ ሆስፒታል አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡-0115572752
የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን
