በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሸን አገልግሎት ዘርፍ በቦንጋ ቅርንጫፍ ተከማችቶ የሚገኘውን ሩዝ የምግብ እህል ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሩዝ የምግብ እህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-የግ/ው/ሽ/ሜ/ሕ/ዘ/ግጨ /ሽ04/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሸን አገልግሎት ዘርፍ በቦንጋ ቅርንጫፍ ተከማችቶ የሚገኘውን ሩዝ የምግብ እህል ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት(ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል እና በመንግሥት ግዥ መመሪያ መሰረት በመንግሥት ግዥ አቅርቦት የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። የዕጣን ምርቶች ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል፡፡
4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሐሙስ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10:30 እንዲሁም ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-5:30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10:30 ሰዓት በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩከ ፊትለፊት በኢግሥኮ የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 በመቅረብ መገዛት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርሩ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው ዝርዝር መሰረት መጫረት ይቻላል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራቾ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
8. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙስም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዲስ አበባ፡- 011470-84-75/0116 66-23-90
አዳማ፡- 022111-21-22/0221-11-31-56
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና የሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ
