የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ባለበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር መአኤ/01/2018
የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ንብረትነታቸው የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ባለበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በሟሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ውስጥ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡
3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎቹ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒአ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡ የዕቃዎቹ የመነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) ያላስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፤
5. ጨረታዉ መጋቢት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መዝናኛ ክበብ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 2 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።
7. የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ባወጣው ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን በሦስት ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልከ ቁጥር 011-2-76-52-94 ወይም 011-2-78-30-08 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
10. የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት
