የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ለሱቅ እና ለመጋዘን ኪራይ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ
የግዥው አይነት
ሎት 1 ለሱቅ እና ለመጋዘን ኪራይ ግዥ
1. በዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያለውና የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፡፡
2. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር) ወይም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ስም CPO (ጋራንትድ ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ የሚችሉ ፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 1000 /አንድ ሺህ ብር / በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ቢሮው በሰጣችሁ ፎርማት ላይ በመሙላት እና የድርጅታችሁ ማህተም፣ ፊርማና ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ፡-
6.1. ፋይናንሽያል አንድ ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል አንድ ኮፒ፡፡
6.2. ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በተለያዩ ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ - ዓርብ ከ2፡30 – 11፡0 ሰዓት ድረስ የግዥ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 803 በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸኋል፡፡
8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ማለትም የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት (ማቅረብ) አይቻልም፡፡
10. ቢሮው ብዛቱን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ በገለጽነው መሰረት መቀነስና መጨመር የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:
ለተማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118126179/ 0111703024/ በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ውቤ በረሃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ
