የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ነገሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
· ሎት 1. ሲሚንቶ
· ሉት 2. የፋብሪካ ማቴሪያል በሰቆጣ ቃልኪዳን በጀት
· ሎት 3. የእንስሳት መድሀኒትና የላብላቶሪ እቃዎች
· ሉት 4. የመኪና ጎማ
ከተራ ቁጥር 1- 4 የተዘረዘሩትን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት
1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር ያላቸው
4. የግዥ መጠኑ 200,000,00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ሻት ከፋይ መሆን አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
7. የጨረታው ሰነድ ከደሴ ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ለእያንዳንዳቸው ሰነድ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው ከ05/07/2018 ዓ.ም እስከ 19/07/2018 ዓ.ም በአየር ላይ ይውላል፡፡
9. ጨረታው በ21/07 /2018 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
10. ተጫራቾች ኦርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉበትን እቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው።
11. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔፍኬሽን /ናሙና የጨረታ ሰነድ ሲገዙ ማየት (ማግኘት) ይቻላል፡፡
12. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ በሎት ስለሆነ ሙሉ በሙሉ መሙላትና ለእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው።
13. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ለሚያቀርቡት ዕቃ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በጽ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት፡፡
14. ተሸናፊ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ያስያዙት 2% ሲፒኦ ከአምስት ቀን በኋላ ይመለስላቸዋል።
15. አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያሲዝ ይሆናል፡፡
16. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ በየሴክተሩ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
17. በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ እስከ 21/07/2018 ዓ.ም ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 3:30 ሰዓት ድረስ እንዲያስገቡ እየገለፅን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
18. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ ዙ/ወ/ግዢ/ቢሮ በተዘጋጀው ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-11-77-63 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
19. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
20. እያንዳንዳቸው መድሀኒት የጊዜ ቆይታ ሁለት አመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ድርጅት /ተጫራች/ ኦርጅናል እቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። እንዲሁም ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ምንአልባት ቢሰረዝ እንኳን ፓራፍ ማድረግ ይኖርበታል።
ስልክ ቁጥር 033 111 77 63 ይደውሉ።
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
